https://youtu.be/gu6w_VEnop4 Renewed night clashes break out outside Lebanese parliament | AFP Jan 23, 2020
Posts
- Get link
- X
- Other Apps
የስብዕና መዛባት (Personality Disorders) በዓለም ላይ ከሚኖሩ አጠቃላይ ህዝቦች ውስጥ ከ 1-20% የሚያህሉት ለተለያዩ ዓይነት የስብዕና መዛባት ችግሮች ተጋላጭ ናቸው፡፡ የስብዕና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስንል ወደ አእምሯችን የሚመጣው መንገድ ላይ ጨርቁን ጥሎ የሚሄደው፤ አማኑኤል ሆስፒታል የተኛችው ፤ ወይም ደግሞ ሰውን በአረመኔያዊ ሁኔታ ገድሎ እስርቤት ውስጥ በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቀው ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በዓለም ላይ በጣም በጥቂቱ ከ 25 ሰው አንዱ ለተለያየ ዓይነት የስብዕና መዛባት ተጋላጭ ሲሆን፤ እነዚህ ሰዎች የቤተሰባችን አካል፤ ጎረቤት፤ ወይም ደግሞ የስራ ባልደረቦቻችን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ለስብዕና መዛባት ዋና መንስኤዎች የትወልድ ሃረግ (Genettics) ፤ በልጅነት ዕድሜ የሚደርስ አካላዊ፤ ወሲባዊና ስነልቦናዊ ጥቃት፤ እንዲሁም ያደግንበት ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው፡፡ የስብዕና መዛባት ያለባቸው ሰዎች በአጠቃላይ በሶስት ቡድን (Clusters) ይከፈላሉ፡፡ ቡድን ሀ የስብዕና መዛባቶች (Cluster A Personality Disorders) 1. በምክንያት ያልተደገፈ ጥርጥር እና ከመጠን ያለፈ ሰዎችን ያለማመን ችግር (Paranoid Personality Disorder) ፡ - እነዚህ ሰዎች ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ የትዳር ጓደኛቸው ከሌላ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው ብለው ሊያምኑ ይችላሉ፡ ከአስር አመት በፊት ወልደው ያሳደጉትን ልጅ ...