የስብዕና መዛባት (Personality Disorders)
በዓለም ላይ ከሚኖሩ አጠቃላይ ህዝቦች ውስጥ ከ 1-20% የሚያህሉት ለተለያዩ ዓይነት የስብዕና መዛባት ችግሮች ተጋላጭ ናቸው፡፡ የስብዕና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስንል ወደ አእምሯችን የሚመጣው መንገድ ላይ ጨርቁን ጥሎ የሚሄደው፤ አማኑኤል ሆስፒታል የተኛችው ፤ ወይም ደግሞ ሰውን በአረመኔያዊ ሁኔታ ገድሎ እስርቤት ውስጥ በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቀው ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በዓለም ላይ በጣም በጥቂቱ ከ 25 ሰው አንዱ ለተለያየ ዓይነት የስብዕና መዛባት ተጋላጭ ሲሆን፤ እነዚህ ሰዎች የቤተሰባችን አካል፤ ጎረቤት፤ ወይም ደግሞ የስራ ባልደረቦቻችን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ለስብዕና መዛባት ዋና መንስኤዎች የትወልድ ሃረግ (Genettics)፤ በልጅነት ዕድሜ የሚደርስ አካላዊ፤ ወሲባዊና ስነልቦናዊ ጥቃት፤ እንዲሁም ያደግንበት ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው፡፡ የስብዕና መዛባት ያለባቸው ሰዎች በአጠቃላይ በሶስት ቡድን (Clusters) ይከፈላሉ፡፡
ቡድን ሀ የስብዕና መዛባቶች (Cluster A Personality Disorders)
1. በምክንያት ያልተደገፈ ጥርጥር እና ከመጠን ያለፈ ሰዎችን ያለማመን ችግር (Paranoid Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ የትዳር ጓደኛቸው ከሌላ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው ብለው ሊያምኑ ይችላሉ፡ ከአስር አመት በፊት ወልደው ያሳደጉትን ልጅ የእኔ አይደለም ብለው ሊክዱ ይችላሉ፤ ዙሪያ ገባውን ሁሉ በጥርጣሬ የሚመለከቱ እና ሰዎቸ በመሰረቱ አደገኞች ናቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው፤ ለእነዚህ ሰዎች በቅንነት የወረወራችሁት ሃሳብ እንደ ጥቃት ሊቆጠር ይችላል
2. ከውጪዉ ዓለም ወይም ከእውነታው ሸሽተው በራሳቸው
አለም (ሃሳብ) የሚኖሩ (Schizoid Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች በራሳቸው ዓለም አብዝተው የሚመሰጡ፤ በእውኑ ዓለም ተጨባጭ ያልሆኑ ሃሳቦችን የሚያልሙ ሲሆን ለማኅበራዊ ደንቦች ግድ የሌላቸውና ከሰዎች ጋር ስሜታዊ ትስስር ለመፍጠር ፍላጎት የሌላቸው ናቸው
3. በአነጋጋራቸው፤ በባህሪያቸው፤ በአስተሳሰባቸው ላይ መዛባት ያለባቸው ሰዎች (Schizotypal Disorder):-
እነዚህ ሰዎች ከሌሎቹ የስብዕና መየስብዕና መዛባት (Personality Disorders)

እነዚህ ሰዎች ከሌሎቹ የስብዕና መዛባት ዓይነቶች በተለየ መልኩ በቀላሉ ችግር ውስጥ እንደሆኑ በአነጋገራቸው፤ ከተለመደው ወጣ ባለው ባህሪያቸው እንለያቸዋለን፡፡ ምንአልባትም በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ እንደ “እብድ” የምንቆጥራቸው አብዛኞቹ የእዚህ ስብዕና መዛባት ተጋላጮች ናቸው
ቡድን ለ የስብዕና መዛባቶች (Cluster B Personality Disorders)
1. ለማኅበረሰብ ህግና ደንቦች ግድ የሌላቸው (Antisocial Personality Dsiroder)፡-
ሌሎች ሰዎች ላይ ሆን ብለው አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት የሚያደርሱ፤ ርህራሄ የሌላቸው እና የሰዎችን ስሜት የማይረዱ፤ ባጠፉት ጥፋት መጸጸት የማይሰማቸው እና ከህይወት ተሞክሮ ትምህርት ወስደው ራሳቸውን ለማሻሻል የማይሞክሩ ናቸው:: ብዙ ጊዜ ጥቃት አድርሰው፤ወንጀል ፈጽመው ወደ ህግ ሲቀርቡ ብናያቸውም አብዛኞቹ ግን በረቀቀ መንገድ የሚንቀሳቀሱ፤ ከህግ ከለላ በቀላሉ የሚያመልጡና በዕለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ሰዎች ናቸው
2. ስለራሳቸው ማንነት ማወቅ የተቸገሩ (Boarderline Personality
Disorder):-
እነዚህ ሰዎች አበዝተው ባዶነት፤ የስሜት አለመረጋጋትና ፍርሃት የሚሰማቸው ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ቁጡዎች፤ ራሳቸውን ለመጉዳትና ለማጥፋት የሚሞክሩ ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የስብዕና መዛባት በልጅነታቸው የጾታ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ላይ የተለመደ ነው፡፡
3. በሰውነታቸው ያላቸውን መልካም ዋጋ የማይረዱ (Histrionic Personality Disorder)፡-
እነዚህ ሰዎች የሌሎችን ትኩረት አብዝተው የሚሹ እና በዕቅዳቸው ሁሉ የሌሎችን አበረታችነት የሚጠብቁ ናቸው:: ሌላ ሰው ቀጥሉ ካላላቸው ምንም ዓይነት ውሳኔ ለመወሰን ይቸገራሉ፡፡ከመጠን በላይ ለውበታቸውና ለአለባበሳቸውም የሚጨነቁም ናቸው
4. ክፉ ሰዎች (Narcissistic Personality Disorder)፡-
ሲበዛ ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎች፤ በነገሮች ሁሉ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሰሉና በጣም ተቆጣጣሪዎች ናቸው፡፡ የዚህ ስብዕና መዛባት ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሌሎችን የሚቀርቡት በሆነ መንገድ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ሲያስቡ ብቻ ነው፡፡ እነሱ የፈለጉት ነገር ካለሆነ ለበቀል የሚጋበዙ ፤ዓለም በእነሱ ዛቢያ ብቻ የምትሽከረከር የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ቡድን ሐ የስብዕና መዛባቶች (Cluster C Personality Disorders)
1. ከማኅበራዊ ህይወት ራሳቸውን የሚያገሉ (Avoidant Personality Disorder)፡-
ሲበዛ የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው በዚህም ምክንያት ሰዎች ስለነሱ መጥፎውን እንደሚያወሩ የሚያስቡ፤ ሰዎች የወቀሷቸውና ያገለሏቸው የሚመስላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ራሳቸውን ከማኅበራዊ ህይወት ያገላሉ፡፡ ሰርግ እና ሃዘን ቤት መሄድ፤ ከጓደኞች ጋር ሻይ ቡና ማለት ያስጨንቃቸዋል፡፡
2. በሌሎች ሰዎች ላይ ሲበዛ ጥገኛ የሆኑ ሰዎች (Dependent personality Disorder)፡- በራሳቸው
መተማመን የሌላቸው፤ በዕለት ተዕለት ኑሯቸው ውስጥ የሌሎችን ውሳኔ የሚጠብቁ፡ ሲበዛ ሽቁጥቁጥና ለሰው አጎብዳጅ የሆኑ ሰዎች ናቸው
3. ስህተት አልባ ህይወት ፈላጊዎች (Anankastic Personality Disorder)፡- ለህጎች
፤
ስርአቶች ፤ ዕቅዶች ሲበዛ አብዝተው የሚጨነቁ፡፡ ያቀዱት ጉዳይ ካልተፈጸመ ዕረፍት የሚነሳቸው፤የሚለብሱት ልብስ መዛነፍ ወይም አለመተኮስ ቀኑን ሙሉ የሚረብሻቸው ሰዎች ናቸው፡፡
(በሰብለወንጌል አይናለም)
@Zepsychologist
Comments
Post a Comment